Bíblia OnLine

Nova Pesquisa         Todo o Livro         Todo o Capítulo

   Versão: Ethiopian: Amharic (NT)
 
Mateus 4:23ኢየሱስም በምኩራቦቻቸው እያስተማረ የመንግሥትንም ወንጌል እየሰበከ በሕዝብም ያለውን ደዌና ሕማም ሁሉ እየፈወሰ በገሊላ ሁሉ ይዞር ነበር።    
Mateus 4:24ዝናውም ወደ ሶርያ ሁሉ ወጣ፤ በልዩ ልዩ ደዌና ሥቃይም ተይዘው የታመሙትን ሁሉ አጋንንትም ያደሩባቸውን በጨረቃም የሚነሣባቸውን ሽባዎችንም ወደ እርሱ አመጡ፥ ፈወሳቸውም።    
Mateus 4:25ከገሊላም ከአሥሩ ከተማም ከኢየሩሳሌምም ከይሁዳም ከዮርዳኖስም ማዶ ብዙ ሕዝብ ተከተሉት።    
Mateus 5:1ሕዝቡንም አይቶ ወደ ተራራ ወጣ፤ በተቀመጠም ጊዜ ደቀ መዛሙርቱ ወደ እርሱ ቀረቡ፤    
Mateus 5:2አፉንም ከፍቶ አስተማራቸው እንዲህም አለ።    
Mateus 5:3በመንፈስ ድሆች የሆኑ ብፁዓን ናቸው፥ መንግሥተ ሰማያት የእነርሱ ናትና።    
Mateus 5:4የሚያዝኑ ብፁዓን ናቸው፥ መፅናናትን ያገኛሉና።    
Mateus 5:5የዋሆች ብፁዓን ናቸው፥ ምድርን ይወርሳሉና።    
Mateus 5:6ጽድቅን የሚራቡና የሚጠሙ ብፁዓን ናቸው፥ ይጠግባሉና።    
Mateus 5:7የሚምሩ ብፁዓን ናቸው፥ ይማራሉና።    

   
Veja também: CvvNetPágina anterior    [ 1 2 3 4 5 6 7 8 9 10 11 12 13 14 15 16 17 18 19 ]    Última página